Adaretube Large Entertainment Website
Welcome
Login / Register

በቀን ህዳር11/2011 ዓ/ም ከኤጄቶ የተሰጠ የአቋም መግለጫ - Ejjeetto 9 points resolution on Nov 20 2018 - Hawassa - Must Read!

====================================
የሲዳማ ህዝብ በ130 ዓመታት የትግል ታሪክ ራሱን በራሱ በማስተዳደር በኢትዮጵያ ካሉ መንግስታት አንዱ ሆኖ ለሐገር ዕድገትና አንድነት የበኩሉን ለመወጣት የሞት፤የእስራት፤የስደትና ሌሎች ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችም በበርካታ ዜጎቹ እየተፈጸሙበት መቆየታቸዉ ሃቅ ነዉ፡፡ ህዝባችን ይህንን ፍዳ እንዲቀምስም ምክንያት የሆኑ ከራሱ አብራክ የወጡ ባንዳዎችና ሌሎች የሲዳማን እሴት የማያዉቁ መሆናቸዉን በመገንዝብ በጽኑእ እየታገለ መምጣቱን ሰማዕታቱ ምስክሮች ናቸዉ፡፡

 በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በልዩ ሁኔታ የህዝቡ ጥያቄ መሥመር እንዲገባ ህዝቡ በምክር ቤቱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ በህ-ገመንግስቱ መሠረት ሪፈረንደም መካሄድ እዳለበት ቢታወቅም ሳይደራጅ ወራቶች በመቆጠራቸዉ ይህንን ተግባር የሚመለከታቸዉ ሁሉ በፍጥነት ማድረግ እንዲችሉ ኤጄቶ አቋሙን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ ዛሬ በቀን ኅዳር 11/2011 ዓ.ም ያስተላልፋል፡፡

1. በሲዳማ ዞንና በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ያለዉ ከከፍተኛ አመራር እስከ ቀበሌ ድረስ ያለዉ ሪፎርም በአስቸኳይ የሐገራዊዉን እይታ መሠረት በማድረግ እንዲካሄድ በሙሉ ድምጽ ተስማምተናል፡፡ይህ ለዉጥም የህዝብ ዉግንና ያላቸዉ፤የህዝብ ችግር የወላዳቸዉ፤ከሌብነትና ከጠባብነት ራሳቸዉን ያጸዱ፤የተሸለ የትምህርትና ብቃትና ክህሎት ያላቸዉ፤በስነ-ምግባርና በሥራ ምስጉንነታቸዉ ብቻ የታነጹ እንዲሁም ወጣቱትን ኃይል መሠረት ያደረገ ሪፎርም እንዲደረግ በትጋት እንሠራለን፡፡

2. የሪፈረንደም ጉዳይ በእጅጉ ፈጥኖ የማይካሄድበት ሁኔታ ተፈጥሮ ሲገኝ ቀጥለን ለምንወስደዉ እርምጃ መንግስት ሙሉ ሐላፊነት ይወስደላ፡፡ይህም በሁሉም የሲዳማ ዞንና የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን ተግባራዊ እንዲሆን የሲዳማ ኤጄቶ አባላት ባሉበት ሥፍራ ሁሉ ሆነዉ ተግባራዊ በሚደረግበት ሂደት ላይ ለመትጋት ቃል እንገባለን፡፡

3. በኢትዮጵያ ሐገራችን እየታየ ያለዉ ለዉጥና ሌቦችን በማጋለጥ ለሕግ የማቅረብ ጉዳይ በሲዳማ እና በሲዳማ ዋና ከተማ ባሉ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ላይም እንዲረግ በትኩረት ለመስራትና ለመከታተል ቃል በመግባት የኤጄቶ አባላትም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተወሰደ ላለዉ እርምጃ የለዉጥ ድጋፉን በሰላማዊ ሰልፍ ይገልጻል፡፡

4. የኤጄቶን አንድነት፤ትጋት፤ጽንአትና ሐገር ወዳድነትን እንደጠላትነት ለማየትና በክፉ ለመፈረጅ የሚደፍሩ የመንግሥት ሹማምንቶች፤ግለሰቦች፤የነጋዴዉ ማኅበረሰብና ማንኛዉም ሠራተኛ ከእኩይ ተግባሩ እንዲቆጠብ አጥብቀን ለመቃወምና የህዝብ ወገንተኝነታችንን የበለጠ ለማጠናከር ቃል እንገባለን፡፡

5. የሲዳማ ኤጄቶ የህዝብ ልብ፤ጆሮና ዓይን በመሆን በልማት፤በመልካም አስተዳደርና በክፉ አስተሳሰቦች ዙሪያ በበጎ መንገዶች በመጓዝ ሰላምን የማስፈን አጀንዳ ያለዉ በመሆኑ በሲዳማ ምድር የሚኖሩ ማንኛቸዉም ኢትዮጵያዉያን እንደጓዳቸዉ ወጥተዉ የሚገባበትን ሁኔታ የሚፈጥር ስለመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲያዉቅ የሰላም ታጋይነቱ እንዲቀጥል ቃል እንገባለን፡፡

6. የሲዳማ ዞን መንግሥት የህዝብን አንድነት፤ የኤጄቶን የህዝብ ወገንተኝነትን ለመሸርሸር የታስክ ፎርስና የምሁራን ማኅበር በማለት በግለሰቦችና በቡድኖች ያደራጃቸዉን ጸረ-ሲዳማ የሆኑትን በሙሉ በጥቂት ቀናት ጊዜ ዉስጥ በማፍረስ ለህዝብ ይፋ እዲያደርግ እና በሲዳማ ኤጄቶ ሙሉ ዕዉቅና ያገኙ ግሰለቦች የህዝባችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊወስን የሚችልን ሰነድ እንዲያዘጋጁ ኮሚሽኑን የሲዳማ ዞን እንዲያቋቁም የህዝባችንን ዓላማ በማንገብ ለተግባራዊነቱ በጽናት ለመታገል ቃል እንገባለን፡፡

7. የሲዳማ የህዝብ ጥያቄ ዳር እንዳይደርስ በግልም ሆነ በቡድን፤እንዲሁም ማንኛዉም የፖለቲካ ፓርት አመራሮች የህዝቡን ጥያቄ የኋሊት እንዲጓተትና ወቅቱን ያልጠበቁ ዉሃ የማደፉ አጀንዳዎችን ለህዝብ በማምጣት የሪፈረንደሙ ሂደት እንዲዘገይ የሚያደርጉ፤አንድነትን የሚሸረሽሩ፤የሲዳማ ህዝብ ያወገዛቸዉ ገዳይና አስገዳይ የነበሩትን እንደጀግና በማሰብ በህዝቦች መካል ግጭቶች እንዲፈጠሩ የሚያደርጉ መሪወችና ተመሪዎችም የህዝብ ልጆች አለመሆናቸዉን በማሳወቅ የሲዳማን ሃላሌ መነሻ በማድረግ ሤራ ለመጣል ቃል እንገባለን፡፡

8. የስዳማና የኦሮሞ ህዝብ አንድነትና አጋሪነት የበለጠ የሚጠናከር ስሆን በሁለቱም ህዝብ መካከል ለዉጡን ለመቀልበስ ብለዉ በህዝቦች መካከል ግጭት እየፈጠሩና ለመፍጠር የሚሯሯጡ አካላትን ኤጄቶ በጽኑ እያወገዘ የተፈጠረዉን ችግር በፍጥነት ወደ ሰላማዊ መንገድ እዲመለስ ኤጄቶ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለዉን ወንድማማችነቱን ለማጠናከር ቃል እንገባለን፡፡

9. የሲዳማና ወላይታ ህዝቦች የጋራ ጠላት ያላቸዉ ህዝቦች እንጅ እርስ በእርስ በጠላትነት የሚፈላለጉ እና ጦርነት የገጠሙ ህዝቦች ዘይደሉም፡፡ ይሁን እንጅ በሁለቱም ህዝቦችና ከዉጭ ሀይልም የፖለቲካ ጥቅም ግጭትን መሰረት ያደረገ መናቆርና ግጭትን በተወሰኑ ቡዱኖች ላይ እንድከሰት ያደረጉ ብሆን አሁንም እነዚህ ሀይሎች በህዝብና በሀገር ደረጃ የሰሩትን ወንጀል በህዝብ ካባ ዉስጥ ገብተዉ ለመደበቅ ብለዉ የሚያደርጉትን ሽሽት ህዝብ የመደበቂያ ዋሻ ሆኖ እንዳይቀጥል አጥፊዎች በህግ ፊት እንድቀርቡ በስመ ህዝብ እርቅ ሽፋን እንዳይደበቁ ኤጄቶ በጽናት ይታገላል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ፡፡ ሰላም፤ዕድገትና ብልጽግና ለምድራችን ይሁን፡፡

#ሆላ_ሃላሌሆ!!!! ኅዳር 11/2011 ዓ.ም 

ሲዳማ #ኤጄቶ!!!

 

Source: Ejjeetto ( https://www.facebook.com/samuel.belayneh.7/posts/1374845659319019

 

Related Articles

RSS